በማይናማር መፈንቅለ መንግስት ተካሄደ::

የማይናማር ጦር መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ የሀገሪቱን መሪ ኡንግ ሳን ሱ ኪን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ከመሪዋ በተጨማሪ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በጦሩ መያዛቸው ነው የተገለጸው፡፡

ስልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደሩ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን ይፋ አድርጓል፡፡

የመንግስት ግልበጣው የተሰማው በሲቪል አመራሩና በወታደሩ መካከል ከምርጫ ጉዳይ ጋር በተያያዘ እሰጣ ገባ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ማይናማር እስከ ፈረንጆቹ 2011 ድረስ በወታደራዊ አገዛዝ ውስጥ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡

ሃገሪቱ ባለፈው ህዳር ወር ሁለተኛ ምርጫዋን ያካሄደች ሲሆን በምርጫው የአሳን ሱ ኪ ፓርቲ በሰፊ ድምጽ እንዳሸነፈ ይታወቃል፡፡

የሰላም የኖቤል ተሸላሚዋ አሳን ሱ ኪ ከፈረንጆቹ 1989 ጀምሮ እስከ 2010 ድረስ ለ15 ዓመታት በእስር ቆይተዋል፡፡

አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት የመንግስት ግልበጣውን በመቃወም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ