በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ከተማ በተቃዋሚ ትዕይንት አድራጊዎችና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ

በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ከተማ በተቃዋሚ ትዕይንት አድራጊዎችና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ፡፡በግጭቱም ፖሊስ ትዕይንተ ሕዝብ አድራጊዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የወረወረ ሲሆን ተቃዋሚዎቹም በእጃቸው የገባን ነገር ሁሉ ፖሊስ ላይ ወርውረዋል፡፡ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው በብሩክሊን ሴንተር ፖሊስ አንድ ጥቁር ወጣትን በጥይት ከገደለ በኋላ ነው፡፡ ዳውንት ሙራይት የተባለው ወጣት የ20 ዓመት ወጣት ሲሆን በጥይት የተገደለውም የትራፊክ መብራት አካባቢ ነው፡፡የብሩክሊን ሴንተር ከንቲባ በከተማይቱ ሰዓት እላፊ ያወጁ ሲሆን ነዋሪውም በቤቱ ተሰብስቦ እንዲቀመጥ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡ በዚችው ከተማ በነጭ ፖሊስ የተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጉዳይ አሁን በፍርድ ቤት እየታየ ሲሆን በዚሁ ምክንያት ከተማይቱ ውጥረት ውስጥ መግባቷን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡