በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኒውዮርክ ታይምስ እና ሲ ኤን ኤን ቢሮዎች በመገኘት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኒውዮርክ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት፣ በኒውዮርክ ታይምስ እና ሲ ኤን ኤን ቢሮዎች በመገኘት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ሰልፈኞቹ የመንግስታቱ ድርጅትና ሌሎችም አካላት በጽንፈኛው የህወሓት ደጋፊዎች የሚሰራጨውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ተመርኩዘው በኢትዮጵያ ላይ ለመፍጠር እየሞከሩ ያለውን ያልተገባና ኢ- ፍትሃዊ ጫና እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ሲ ኤን ኤን እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚዲያ ተቋማትም ያልተጨበጠ መረጃን ተንተርሰው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረርና ከእውነት የራቁ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ድምጻቸውን አሰምተዋል።መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን ህግ የማስከበር እርምጃ እንዲሁም በትግራይና በሌሎች አካባቢዎች እያደረገ ያለውን የሰብዓዊ እርዳታና የመልሶ ማቋቋም እርምጃ እንደሚደግፉም ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።አሜሪካ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር በፍትሃዊነት እንዲቋጭ እና ሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ለቃ እንደትወጣ አዎንታዊ ሚና እንድትጫወትም ሰልፈኘኞቹ ጠይቀዋል።