#በአዲስ አበባ የተመዘገቡት መራጮች 200 ሺህ 903 ብቻ ናቸው ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

#በአዲስ አበባ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን የተመዘገቡት መራጮች 200 ሺህ 903 ብቻ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ በመጪው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከሚሳተፉ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ትላንት ባደረገው ምክክር ላይ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ከምርጫ ጣቢያዎች አለመከፈት በተጨማሪ የተመዝጋቢዎች ቁጥርም እምብዛም መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማን ለአብነት በመጥቀስ ገልጿል፡፡በዚህም ከ200 ሺህ ብዙም የዘለለ አይደለም ከተባለው የአዲስ አበባ ከተማ የመራጮች ምዝገባ ቁጥር ባለፈ እስካሁን ድረስ ምርጫ ጣቢያዎች ያልተከፈቱባቸው ክልሎችና አካባቢዎች ተገልጸዋል፡፡ እነዚህም በኦሮሚያ ክልል አራቱ የወለጋ ዞኖች፣ በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም በደቡብ ክልል ቤንች ሸካና ጉራፈርዳ ብሎም የሶማሌና አፋር ክልሎች ናቸው ያለው ቦርዱ የፀጥታ መደፍረስና የትራንስፖርት እጥረትን ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብሏል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs