#በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መራዘሙ ሲነገር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ደግሞ በታህሳስ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ8ኛና የ12 ክፍል ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥተዋል።

በመግለጫው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ የተገለጽ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል ተብሏል።

ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁም ነው ማሳሰቢያ የተሰጠው። መረጃውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር ማህበርዊ ትስስር ገጽ ላይ ነው።#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs