News

በጤና ኤክስቴንሽን ላለፉት 14 አመታት 17 ሺህ በላይ ዜጎችን ተረድተዋል ተባለ

በጤና ሚኒስቴርና ጄ.ኤስ.አይ ኢትዮጵያ በተባለ የግብረ ሰናይ ድርጅት እንዲሁም በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አጋርነት ላለፉት 14 ዓመታት ለተሰሩ የጤና ኤክስቴንሽን ስራዎች የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ።
14 አመታትን የዘለቀውና ላስት ቴን ኪሎ ሜትር የተሰኘው የጄ.ኤስ.አይ ፕሮጀክት በመጀመሪያ ደረጃ ህክምና፣ በእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ጤናና በሌሎችም የጤና ዘርፎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የቆየ ሲሆን በዚህም 17 ሚሊዮን ያክል ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ሰምተናል።
ፕሮጀክቱ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በትግራይ ክልሎች በሚገኙ 240 ወረዳዎች ባሉ 5 ሺህ ቀበሌዎች መከናወኑ የተገለጸ ሲሆን 10 ሺህ ያህል የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችና ከ100 በላይ ድጋፍ ሰጭ ሴቶችን በማሰልጠን በቅድመና ድህረ ወሊድ እንዲሁም በወሊድ ጊዜ የሚያስፈልገውን የጤና ሽፋን ከፍ ለማድረግ እንደተቻለም ተገልጿል። ዜናው የሪፖርተራችን ሰላማዊት ሽፈራው ነው፡፡