#ትራምፕ የስልጣን ርክክብ ለማድረግ ተስማሙ።

የምርጫው ድምጹ ተጭበርብሯል፣ ምጫውን እኔ ነኝ ያሸነፍኩት፣ ዳግም ድምጽ ቆጠራ ይደረግ በማለት ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልነበሩት የአሜሪካው ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መደበኛው የስልጣን ርክክብ ለተመረጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደል እንዲካሄድ መፍቀዳቸው ተነግሯል።

የአሜሪካ አጠቅላይ አገልግሎት አስተዳደር/GSA/ ጆ ባይደን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ዳግም ይፋ ያደርገ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተቋሙ ማድረግ የሚገባውን የስልጣን ርክክቡ እንዲከውን ፈቅደዋል።

ተመራጪ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደ ፈረንጆቹ ጥር 20 ቃለ መሀላ ፈጽመው በይፋ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ቢቢሲ ነው የዘገበው።#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs