ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኒውሮ ሳይካትሪስት ፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ የ2022 የአልዛይመር አዋርድን አሸነፉ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኒውሮ ሳይካትሪስት ፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ የ2022 የአልዛይመር አዋርድን አሸነፉ
በጆርናል ኦፍ አልዛይመር ዲዚዝ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ጆርናል በሚዘጋጀው አመታዊ የጥናትና ምርምር ስራ በአልዛይመር ወይም የመርሳት ችግር ላይ ከተሰሩ ጥናቶች የላቀ ሆኖ በመገኘቱ ነው የዘንድሮ ተሸላሚ የሆኑት፡፡
ጥናቱን ከዶክተር ጃኒና ኬል ሮሽ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ በዶክተር ኦፍ ሜዲስን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን ለ25 አመታት በአሜሪካ ሃገር በሚገኘው ማዮ ክሊኒክ ውስጥ ሲያገለግሉ እንደቆዩና በአሪዞና ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን መቀበላቸው ተነግሯል፡፡
የተመረጠው ጥናት ባለቤቶች 7 ሺህ ዶላርና የብር ሜዳሊያ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ሲነገር የሽልማት ስነ-ስርዓቱም በቀጣዩ ነሃሴ 14/2014 ዓ.ም ላይ እንደሚካሄድ ገልጿል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS