አንጋፋው የቲያትር ባለሞያ ረ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 አመታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ረ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ የቲያትር መምህር፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ አዘጋጅና ተርጓሚ እንዲሁም በርካታ መጽሀፍቶችን ለአንባቢያን ያበረከቱ ሲሆን በትወናቸው እንዲሁ ይታወቃሉ።

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በአርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣የሙያ አጋሮች እንዲሁም አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።