አዲስ ነገር – ማሳሰቢያ ለህገወጥ አካላት
የሃገርን ብሄራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ህገ-ወጥ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ዓለማችንን በጥብቅ ትስስር ውስጥ እንድትቆይ ከሚያስገድዷት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ንግድ ነው ያለው ሚኒስቴሩ በዚህ ትስስር ውስጥ መቆየት የሚቻለው የንግድ ስርዓት በጥሩ ስነምግባር ሲመራ ብቻ እንደሆነ ገልጾ ነገር ግን አሁን ላይ የግል ጥቅማቸውን ብቻ ለማረጋገጥ ጥረት የሚያደርጉ ህገ ወጥ አካላት መበራከታቸውንም አመልክቷል፡፡
መንግስት እየተስተዋለ ያለው የሸቀጦች ዋጋ ንረት በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለማቃለል መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ከውጪ በፍራንኮ ቫሉታ እና ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ማድረጉን በማንሳት በዚህ መንገድ የሚገቡት ምርቶች ግን ለታለመላቸው ዓላማ ከመዋል ይልቅ ለተወሰኑ ህገ ወጥ አካላት የኪስ ማደለቢያ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም አምራቾችና ሸማቾች ሳይሆኑ በግብይት ሂደቱ ውስጥ ምንም እሴት የማይጨምሩ አካላት ብቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበት የተራዘመ የግብይት ስርዓት መኖሩ ለኑሮ ውድነቱ መባባስ መንስኤ በመሆኑ ይህንን ያልተገባ ድርጊት ለማስቆም የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን ዘርግቻለሁ ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዚህ ህገ ወጥ ተዋንያን የሆኑ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ሲል ማሳሰቡን ከማህበራዊ የትስስር ገጹ ተመልክተናል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New