አዲስ ነገር – ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ60 ሚሊዮን ዩሮ የተገነባውን ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ ብቅል አምራች ፋብሪካ መርቀው ከፍተዋል።
በዛሬው ዕለት የተመረቀው የሱፍሌት ማልት ብቅል አምራች ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ስር በሚተዳደረው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባ ሲሆን በ10 ሔክታር መሬት ላይ ማረፉም ተነግሯል፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ፤ የፋብሪካው አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸው የተነገረ ሲሆን ፋብሪካው በአመት 60 ሺህ ቶን ብቅል የማምረት አቅም እንዳለው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ኢንቪቮ ግሩፕ በተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ስር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ፤ 90 የኢንዱስትሪ መንደሮች እና 13 ሺህ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በገነባቸው 28 የብቅል ማምረቻዎች በየአመቱ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ቶን ብቅል ለአለም ገበያ እያቀረበ ይገኛል ተብሏል።
በኢትዮጵያ ያሉት ሁሉም የቢራ ፋብሪካዎች አመታዊ የማምረት አቅማቸው 17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሔክቶ ሊትር ቢሆንም በብቅል አቅርቦት እጥረት እያመረቱ ያሉት 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሔክቶ ሊትር ብቻ መሆኑ ተነግሯል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New