አዲስ ነገር – ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚመጣው ሳምንት የተጠቃሚዎቼን ቁጥር ወደ አንድ ሚሊዮን አደርሳለሁ አለ። አሁን ላይ አጠቃላይ አዲስ አበባን ጨምሮ በ16 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኘው ሳፋሪኮም ከ9 መቶ ሺህ በላይ ደንበኞችን በማፍራት ሥራ በጀመረበት በመስከረም ወር ያገኘው ገቢው 74 ሺህ ዶላር መድረሱን የኬንያው ሲትዝን ዲጅታል ሚድያ ዘግቧል፡፡ ምንም እንኳን መንግስት የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ተቋማት ክፍት ቢያደርግም የሞባይል ገንዘብና መሰል ስራዎች እስካሁን በስራ ላይ እንዲውሉ ፈቃድ አለመሰጠቱን አስታውቆ ወደ ስራ ለመግባት ይቻል ዘንድ ከብሄራዊ ባንክ ጋር በጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New