አዲስ ነገር – አረምን ወደ ሀይል ምንጭ

በአፋርና በአማራ ክልል ብቻ 1.6ሚሊየን ሄክታር መሬት የወረረውን ኘሮሶፊስ ጁሊፎራ አረምን ወደ ሀይል ሰጪ የኢንዱስትሪ ግብአት መለወጥ የሚያስችል ኘሮጀክት በዛሬው እለት በአፋር ክልል በይፋ ተጀምሯል።
በክልሉ አሚባራ ወረዳ የተጀመረው ይህ ኘሮጀክት በከፍተኛ መጠን የተስፋፋውን አረም መቁረጫና መውቂያ በተገጠመላቸው ማሽኖች በመታገዝ ወደ ኢንዱስትሪ ግብአትነት የመቀየር ስራ እንደሚሰራበት ተነግሯል።
አረሙ ከተፈጨ በኋላ ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙትን የድንጋይ ከሰል መተካት እንደሚችል በጥናት ተረጋግጧል የተባለ ሲሆን ወደተግባር ሲገባ በየአመቱ ለድንጋይ ከሰል የሚወጣውን ከ400ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ያስቀራል ነው የተባለው።
የመፍጨትና አረሙን ከስሩ የመንቀል ስራ ለመስራት ሁለት ማሽኖች በአፋር ክልል አንድ የመቁረጫና የመውቂያ ማሽን ደግሞ በሶማሌ ክልል መሰማራታቸውን የሰማን ሲሆን 60ሴንቲሜትር ወደውስጥ በመዝለቅ የአረሙን ስር መንቀል የሚችል ሌላ 1 ማሽን ደግሞ ጅቡቲ ወደብ ላይ መሆኑን ሰምተናል።
እያንዳንዱ ማሽች በቀን 4 ሄክታር መሬት ከአረም ማፅዳት እንደሚችልና መሳሪያዎቹም በአውሮፖ ህብረት ድጋፍ መበርከታቸውን ሰምተናል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New