አዲስ ነገር – አጫጭር የውጭ ዜናዎች
#አሜሪካ ለታዳጊ አገራት የሚውል 1 መቶ 50 ሺ ሜትሪክ ቶን እህል ከዩክሬን ልትገዛ ነው።እህሉ በተለይ በምግብ እጥረት ለተጎዱ አገራት የሚውል መሆኑን የአለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።በተያያዘ ለኢትዮጵያ 23ሺ ሜትሪክ ቶን እህል የጫነችው መርከብ ከ5 ቀናት በኋላ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ዋቢ አድርጎ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
*****
#የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በአሜሪካ ካሉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ምክክር አድርገዋል::መልዕክተኛው በቅርቡ በኢትዮጵያ ያካሄዱትን ጉብኝት አስመልክቶ ለትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በበይነ መረብ ማብራሪያ መስጠታቸውንና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል::
****
በቀድሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን ላይ ክስ መሰረተች ::ክሱን የመሰረተችው ከህግ ውጭ ረዳቶቻቸውን በቁጥጥር ስር በማዋላቸውና ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሌሎች ባለስልጣናትን ስላስፈራሩ ነው። ምንጭ ቢቢሲ።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New