አዲስ ነገር – ኢትዮጵያ ሶማሊያና ፑንትላንድ
ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ፑንት ላንድ የሚገኙበት መልከዓ ምድር ለተመሳሳይ ተፈጥሯዊ አደጋዎች የሚያጋልጥ ነው ያለው የኢፌዴሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር አገራቱ በዚህ ዙሪያ ልምዳቸውን ሊለዋወጡ እንደሚገባ ተናግሯል፡፡
ይህን የተናገሩት የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ሲሆኑ ተቋማቸው እየሰራቸው ባሉ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች ላይ ከፑንት ላንድና ከሶማሊያ ከመጡ የልዑካን ቡድኖች ጋር የልምድ ልውውጥ እያካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ጊዜም የልምድ ልውውጡ የሙያ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ወገኖች ያላቸውን ተመሳሳይ የተፈጥሮ ሃብት በምን መንገድ ማልማት እንደሚችሉ የእውቀት ሽግግር የሚደረግበት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ በቆላማ አካባቢዎች እየተከናወኑ ናቸው የተባሉ ስራዎችን የልዑካን ቡድኖቹ ከነገ ጀምሮ ወደ አፋር፣ ሱማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በማምራት እንደሚመለከቱም ነው የተገለጸው።
በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያና በፑንት ላንድ እየተተገበረ የሚገኘው የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የተሻለ ትግበራ ስለማሳየቱ የአለም ባንክ ስላመነበት የልኡካን ቡድኖቹ ልምድ ለመቅሰም ወደኢትዮጵያ መምጣታቸውም ሲነገር ሰምተናል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ ቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New