አዲስ ነገር – የማስታወቂያ ክልከላ

በአዲስ አበባ ማንኛውም ተሽከርካሪ የድርጅቱንም ይሁን የሌላ ተቋምን አገልግሎት የሚያሳይ ማስታወቂያ ያለ ፈቃድ ለጥፎ እንዳይንቀሳቀስ ተከለከለ
ይህንን ያለው የአዲስ አበባ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ማንኛውንም የውጪ ማስታወቂያዎች ያለ ፍቃድ መለጠፍም ሆነ ማስነገር የሚከለክል መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ የድርጅት አርማ፣ አገልግሎትን የሚያሳይ ጽሁፍም ይሁን ምስል መለጠፍ በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን ባለስልጣኑ ነግሮናል።
እንዲሁም በከተማው የሚገኙ ፈር የለቀቁ የማስታወቂያ አለጣጠፍና አሰራር ስርዓት ለማበጀት እየተንቀሳቀስኩ ነው ያለው ተቋሙ ከአሁን በኋላ በዚህ አይነት ድርጊት ላይ ያለ ፈቃድ የሚሳተፉ አካላት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብሏል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New