አዲስ ነገር – የሰዐት እላፊ በባህርዳር
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት የከተማዋን ህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚያስጠብቁ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተነገሯል ።
ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ከተወሰኑ ልዩ ልዩ መሠረታዊ ውሳኔዎች መካከል የመጀመሪያው የባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን የሚመለከት ሲሆን አሁን ካለንበት ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለከተማችን ሰላምና ደህንነት ሲባል ከሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውም የባጃጅ ወይም ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ ሲል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ቴክኖሎጂ ተጠቅመው የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ውጪ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኃላ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪ ለሚወሰድበት ቅጣትና እርምጃ ኃላፊነቱን ባለቤቱ ወይም አሽከርካሪው እንደሚወስድ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ማንኛውንም ወንጀል መከላከል የሚቻለው የህብረተሰብ የላቀ ተሳትፎ ሲኖር በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተለመደው ጥቆማዎችን በመስጠትና ከህግ አስከባሪዎች ጎን በመቆም ለሰላም ዘብ እንድትቆሙ ሲል የባህርዳር ከተማ አስተዳድር ምክርቤት ጥሪውን ማቅረቡን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New