አዲስ ነገር – የሳይንስ ሙዚየሙ ምርቃት

በአዲስ አበባ የተገነባው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ዛሬ በጠ/ሚር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

ከሙዚየሙ ምርቃት ባለፈም ጠቅላይ ሚስትሩ የቴክኖሎጂ ዐውደ ርእይን አስጀምረዋል። እንዲሁም ለ2 ቀናት የሚቆየው የመጀመሪያው የፓን አፍሪካን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ተከፍቷል። ይኸው ኮንፈረንስ የሚካሄደው ዛሬ በተመረቀው የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ነው ተብሏል።በነገራችን ላይ በአይነቱ አዲስ የሆነውን ይህንኑ በአዲስ አበባ የተገነባው ኢትዮጵያ የሳይንስ ሙዚየም በተመለከተ አንዳንድ መረጃዎች እናካፍላቹ! – በ6.78 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሙዚየሙ ሁለት ግዙፍ ህንጻዎች አሉት።- ትልቁ ህንጻ ከ15 ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።- በሙዚየሙ ውስጥ ቋሚ እና ጊዜያዊ አውደ ርዕይ ማሳያዎች አሉት።- ሙዚየሙ ሳይንስ ጥበባዊ በሆነ መንገድ የሚገለጽበት ጥበብም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚታይበት ነው።- ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ ሆኖ የተገነባው ሙዚየሙ ከጸሐይ ብርሀን የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያገኝ ሲሆን የሙዚየሙ ውጫዊ ክፍል የቀለበት እና የጉልላት ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New