News

አዲስ ነገር – የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሙከራ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድልሬደዋ ከተማ የ2G 3G እና 4G የደንበኞች ኔትዎርክ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ደንበኞች 07 ብሎ የሚጀምረውን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉና የስልክ ጥሪ፣ የዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ከሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንደሚችሉ ተናግሯል።ከዚህም በተጨማሪ የውጪ ሃገር ጥሪዎችን መለዋወጥ እንደሚያስችል ተገልጿል። ደንበኞች ወደ 700 የጥሪ ማዕከል በመደወል በተለያዩ የሃገር ውስጥ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጽ አስታውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New