አዲስ ነገር – የቡና የውጭ ንግድ ክብረ ወሰን

የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢልዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱን የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሀሰን በቲውተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ቡና ባለፉት 10 ወራት ውስጥ የአንድ ቢልዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘቱና ይህ ደግሞ በቡና የውጭ ንግድ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በ2014 በጀት ዓመት ከቡና ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ በየዕለቱ ከ1 ሺህ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ አገራት እየላከች ሲሆን በበጀት ዓመቱ 280 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ አገራት ለመላክ መታቀዱንም የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New