News

አዲስ ነገር – የትምህርት ቤት ምገባ

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የትምህርት ቤት ምገባን እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ፡፡
ጥሪው የቀረበው ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ክላውዴ ጂቢዳር ጋር በተወያዩበት ወቅት ሲሆን ሚኒስትሩ የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአዲስ መልክ የተጀመረውን የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፋ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
እንዲሁም በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ሪፎርሞች መጀመራቸውን እና በትምህርት ቤት ምገባ ዙሪያም እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች መግለጻቸው የተነገረ ሲሆን የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተርም ተቋሙ ከትምህርት ቤት ምገባ በተጨማሪ በርካታ የምግብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
መረጃውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New