አዲስ ነገር – የአይ ሲ ቲ ድጋፍ

ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአ ይ ሲ ቲ ቁሳቁስ ከጀርመን መንግስት በድጋፍ አግኝቻለሁ ሲል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ድጋፉ ከጀርመን መንግስት የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ባንክ የተገኘ ሲሆን በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የአይ ሲ ቲ መሰረተ-ልማት ማስፋፊያ የሚውል እንደሆነና የአይ ሲ ቲ መሰረተ-ልማት ማስፋፊያው በተመረጡ 20 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስረድቷል፡፡

በተጨማሪም የሶፍትዌርና የሀርድዌር ልማት እንዲሁም የቀጥታ የበይነ መረብ ሥልጠናን ጨምሮ በዘርፉ ለሚተገበረው የዲጂታላይዜሽን ሥራ የላቀ ፋይዳ አለው የሚለው ተቋሙ ወደ ሀገር ውስጥ የገባውን ድጋፍ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መጎብኘታቸውን በማህበራዊ የትስስር ገጹ አመልክቷል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New