አዲስ ነገር – የአፍሪካ ህብረት ጥሪ

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር የአፍሪካ ህብረት ይፋዊ ጥሪ አቀረበ ። አፍሪካ ህብረት ያቀረበውን ኦፊሴላዊ ጥሪንም የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ መቀበሉን አሳውቋል፡፡በመንግስት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጽህፈት ቤቱ በኩል ባወጣው የጽሁፍ መግለጫ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ኦፊሴላዊ ጥሪ ማቅረቡን ጠቅሶ ፤ የህብረቱ ግብዣ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ ሆኖ መገኘቱን አመልክትዋል ። ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች ለመውሰድ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን በመጠቆምም ወደፊትም ይህንኑ አጠናከሮ እንደሚቀጥል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ገልጸዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New