News

አዲስ ነገር – የኢሚግሬሽን ማሳሰቢያ

የኢፌዴሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገራት ዜጎችን ህጋዊ የማድረግ ምዘገባ ለመጨረሻ ጊዜ ከነሐሴ 3-10/2014ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ ሲል አሳስቧል።በዚህም በተለያዩ የቪዛ ዓይነት ወደ ኢትዮጵያ የገቡና ቪዛቸው የሚፀናበት ጊዜ ያለፈበት፤የመኖሪያ ፈቃዳቸው የሚፀናበት ጊዜ ያለፈበት፤ ምንም አይነት ቪዛም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞች ፈቃድ ያላቸው ወይም ያለፈቃድ ከተለያየ የስደተኛ ጣቢያ የሚኖሩ የዉጭ ዜጐች ምዝገባው ይመለከታቸዋል።አገልግሎቱ ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የሰጠውት እድል ነው ባለው መግለጫው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በሁሉም ስራ ቀናት ማንነታችሁን የሚገልፅ ሕጋዊ ሰነድ እንደ ፓስፖርት፣ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የስደተኛ መታወቂያ ወይም የምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን ይዛችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ ሲል በማህበራዊ የትስስር ገጹ አሳስቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New