አዲስ ነገር – የኢሰመኮ ማሳሰቢያ
የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችን ያልተከተለና የተስፋፋ እስር ተገቢ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
የፌዴራል መንግሥትና የክልል የፀጥታ ኃይሎች በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች የሚለው ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎችን ከወንጀል ምርመራ በፊትና ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ከማሰር ሊታቀቡ እንደሚገባ አመልክቷል።
ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ያስታወቀው ኢሰመኮ የተወሰኑ ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በቤተሰቦቻቸው የተጎበኙና በተለያየ የጊዜ መጠን ወደ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በርካታ ታሳሪዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውንና፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውንም ጨምሮ ተናግሯል፡፡
በተለይም በአማራ ክልል በርካታ ታሳሪዎች ከመደበኛ መኖሪያ አካባቢያቸውና ከመደበኛ እስር ቦታዎች ውጭ በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን አያውቁም የሚለው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ በማንኛውም አይነት ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እና ቤተሰቦቻቸውም ወዲያው እንዲያውቁ ይገባል ሲል አቤቱታውን አቅርቧል፡፡
በተጨማሪም ኢሰመኮ በማንኛውም ስፍራ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በድንገተኛ ጉብኝት ለመከታተል በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ክትትል በማድረግ ላይ ስለሆነ ሁሉም የፌደራል እና የክልል መንግሥታት አካላት ለኮሚሽኑ ሥራ የመተባበር ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ኮሚሽኑ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ባወጣው ጽሁፍ አሳስቧል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New