አዲስ ነገር – የኢሰመጉ ማሳሰቢያ
በንጹሀን ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አሳስበውኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ኢሰመጉ አስታወቀ።
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዥንጋ ወረዳ ሴነ ቀበሌ በህዝብ እንዳራሴዎች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ቡድን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙንና በብዛት ሴቶችና ህጻናት መሞታቸውን ገልጿል።
ጥቃቱን በመሸሽ በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ በየጫካው ተበታትነው ይገኛሉ የሚለው የተቋሙ መግለጫ ብዙ ቁጥር ያላቸው አስክሬኖች በጅምላ እንደተቀበሩ ከአካባቢው ባገኘሁት መረጃ ለመረዳት ችያለሁ ሲል የተናገረ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ንጹሀን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመትና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል፡፡
በመሆኑም የፌደራል መንግስት፣ የክልል መንግስታት እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት የዜጎችን ደህንነት የማስከበር ተቀዳሚ ሀላፊነታቸውን በቂ ትኩረት ሰጥተው በአግባቡ እንዲወጡ ተቋሙ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New