News

አዲስ ነገር – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ የሚል ሽልማት አገኘ፡፡

ሽልማቱን ያገኘው የግሎባል ትራቭል መጽሄት ባዘጋጀው የ2022 የትራንዚስ አዋርድ የመንገደኞች ምርጫ ነው ።ትራዚስ ትራቭል የተሰኘው ድርጅት የግሎባል ትራቭለርስ እህት ኩባንያ ሲሆን የምርጥ አየር መንገድ ምርጫ የሚያደርገው እድሜያቸው ከ25 እስከ 40 የሚሆኑ ተሳፋሪዎችን በመጠየቅ ነው። በተመሳሳይ አየር መንገዱ ዳግም ወደ ሞስኮ በራራ መጀመሩን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ተናግሯል፡፡አየር መንገዱ በራራውን እንደገና የጀመረው ከስድስት ወር ቆይታ በኋላ ነው።የመጀመሪያ በረራውን ነሃሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ማድረጉን ያመለከተው ኤምባሲው ከዚህ በኋላ በሳምንት ሶስት ጊዜ እንደሚበር ጠቁሟል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New