አዲስ ነገር – የከተማ መለያ ቀለም

መዲናችን አዲስ አበባ የራሷ መለያ የሕንፃ ቀለም ቅብ ሊኖራት ይገባል ተባለ፡፡

ይህ የተባለው የአ.አ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከቂርቆስ ክፍለ ከተማና ከአልሚ ባለሀብቶች ጋር በሕንፃ ቀለም ምርጫ እና የተጀመሩ ህንፃዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ባደረገበት ወቅት ሲሆን በመድረኩ ከተማችን የመለያ ቀለም ሊኖራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ የሕንፃዎች ቀለም በአመዛኙ ምን አይነት እንደሆነ በጥናት የተለየ ሲሆን ለአይን የማይመች የተዘበራረቀና የሚጋጭ ቀለም ያለባቸው በርካታ አካባቢዎች እንዳሉ፤ እንዲሁም ጤንነትን የሚጎዳ መስታወትና አልሙኒየም የሚበዛባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ተመልክቷል፡፡

በመሆኑም የከተማዋ ቀለም ምን አይነት ይሁን በሚለው ዙሪያ እየተሰራ መቆየቱንና የቀለም ቅብ ደረጃ በማውጣት በአከባቢ ከፋፍሎ ሁለት ወይንም ሶስት አይነት ቀለም እንዲኖራትና በዚህም ከተማዋን ውበት ማላበስ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የሚወጣውን ደረጃ የሚጥሱ ሲኖሩ ጠንካራ የሆነ የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት በመፍጠር የእርምት እርምጃ መውሰድ ይገባል መባሉን ከባለስልጣኑ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክተናል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New