News

አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇺🇦 ዩክሬን ‼️የመንግስታቱ ድርጅት የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በዩክሬን ግዙፉ የዛፓሮዥያ የኒውክለር ጣቢያ አካባቢ የደረሰው ፍንዳታ አሳሳቢ መሆኑን አስታወቀ ::በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለው የዩክሬኑ የዛፓሮዥያ የኒውክለር ጣቢያ አካባቢ ላይ እሁድ እለት የተሰማው ፍንዳታ እጅጉን አሳሳቢ በመሆኑ ጥቃቱ ሊቆም ይገባል ሲል የተመድ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አስጠንቅቋል።የሞስኮ እና ኪይቭ ባለስልጣናት ፍንዳታውን አስመልክቶ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑን ሬውተርስ ዘግቧል።

🇮🇩 ኢንዶኔዢያ ‼️በኢንዶኔዥያ በተከሰተው ከባድ የርዕደ መሬት አደጋ በትንሹ 56 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ።በኢንዶኔዢያዋ የጃቫ ደሴት በሬክተር ስኬል 5.6 በተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሞቱት 56 ሰዎች በተጨማሪ ከ 700 በላይ ዜጐች ለጉዳት መዳረጋቸው ነው የተነገረው ::የጃቫ ደሴት በገጠመው በዚሁ የከፋ ርዕደ መሬት በርካታ ህንፃዎች እና የመሰረተ ልማት አውታሮች መውደማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ::

🇹🇷 ቱርክ ‼️ቱርክ በሶሪያ እና ኢራቅ ባሉ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተዘገበ።የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ባወጣው መግለጫ ቱርክ በሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ብቻ በፈፀመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።የቱርክ የመከላከያ ሚኒስቴር በሶሪያ እና ኢራቅ በተወሰደው የአየር ጥቃት ለቱርክ ስጋት የሆኑ የሽብር ቡድን አባላትን እንደደመሰሰ መግለፁን ፍራንስ ቱዌንቲ ፎር ዘግቧል።

🇹🇿 ታንዛኒያ‼️የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ የሚያስተዳድሩት ስታር ሊንክ በታንዛኒያ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት ሊያስጀምር ነው።በስፔስ ኤክስ ኩባንያ ስር የሚመራው ስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ በፈረንጆቹ 2023 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት ለታንዛኒያ አገልግሎት ሊያስጀምር መሆኑን ነው ያስታወቀው።በአፍሪካ የስታር ሊንክ ሳተላይት ኢንተርኔት ተጠቃሚ ከሆኑት ናይጄሪያ እና ሞዛምቢክ ቀጥሎ ታንዛኒያ 3ኛዋ ተጠቃሚ ልትሆን እንደምትችል ዘ ሲትዝን ዘግቧል ::

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New