አዲስ ነገር – ድጋፍ ለሰቆጣ ቃልኪዳን

የቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የ100 ሚሊዮን ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታቋል

የቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የህጻናትን የመቀንጨር አደጋ ለመከላከል በኢትዮጵያ እየተተገበረ ለሚገኘው ለሰቆጣ ቃልኪዳን ተግባራዊነት የሚያግዝ የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ አምባሳደር መለስ አለም የተቋማቸውን ሳምንታዊ መግለጫ በሰጡበት ጊዜ ፋውንዴሽኑ ይህን ቃል የገባው በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 77ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በሰቆጣ ቃልኪዳን ዙሪያ ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው መድረክ ላይ መሆኑን ገልጸዋል ።ጉባኤው በሁለትዮሽና በባለብዙ ዘርፍ መስኮች ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደሆነም አንስተዋል። በሌላ በኩል ከዚሁ ጉባኤ ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተመድ የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮዎች ወደሌሎች 10 አገራት ለማካፈል ፍላጎት እንዳለው ገልጿል ተብሏል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New