አዲስ ነገር – ጳጉሜን በመደመር
በአምስቱ የጳጉሜ ቀናት የተለያዩ መርሃ ግብሮች ይካሄዳሉ፡፡
ጳጉሜ አንድ የበጎ ፍቃድ፣ ጳጉሜ ሁለት የአምራችነት ቀን ፣ጳጉሜ ሶስት የሰላም ቀን፣ ጳጉሜ አራት የአገልጋይት ቀን እንዲሁም ጳጉሜ አምስት የአንድነት ቀን የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸውና እያንዳንዱ ቀናትም ከተሰጠው ስያሜ ጋር የተዛመደ መርሃግብር ይካሄዳል ተብሏል፡፡ጷጉሜን በመደመር የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚሁ መርሀ ግብር ላይ ሰላም ጤና ትምህርት ግብርና ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እንዲሁም አንድነት ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ እንደሚገኙበት ተሰምቷል።አካባቢን የማጽዳት፣ደም የመለገስ፣አረጋዊያንን የመርዳት የሰላም እሴቶችን የማስተማርና ሌሎችም ክንውኖች እንንደሚኖሩም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New