ኢትዮ ሳት እስካሁን ባለው ሁኔታ 60 የአገር ውስጥና የውጪ አገር ጣቢያዎችን በሳተላይቱ ውስጥ ማካተት መቻሉንና አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሳት እስካሁን ባለው ሁኔታ 60 የአገር ውስጥና የውጪ አገር ጣቢያዎችን በሳተላይቱ ውስጥ ማካተት መቻሉንና አስታወቀ፡፡ የዲሽ ሳህኖችን ለማስተካከል እንዲሁም አድራሻውን ለመሙላት 20 ሺህ ወጣቶችን በስራው ላይ እንደሚያሳትፍ አስታወቀ።

ኢትዮ ሳት ይህን ያለው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን ብሮድካስተሮች በኢትዮሳት በኩል ሥርጭት እንዲያደርጉ ለማስቻል የተሰራውን ሥራ አስመልክቶ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።

በዚሁ ጊዜ ኢትዮሳት የአገሪቷ ብሮድካስተሮች ለስርጭት በሚል በዓመት የሚያወጡትን 10 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በግማሽ መቀነስ የሚያስችል አማራጭ ሆኖ መምጣቱ የተነገረ ሲሆን በተጨማሪም ከዚህ በፊት የሚያጋጥመውን የአገልግሎት ሽፋን ችግር መቀነስ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት ያስችላልም ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳለው ኤስ.ኢ.ኤስ ከተባለ የሳተላይት አከራይ ኩባንያ ጋር በተደረገው የውል ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የኢትዮሳት ሳተላይት ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው ያሉት።

ዋና ዳይሬክተሩ ይህ አሰራር የአገሪቷ የቴሌቪዥን ቻናሎች የተሻለ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የወጪ ጫናቸውንም መቀነስ ያስችላል ያሉ ሲሆን የተመረጠው ሳተላይት አከራይ ድርጅትም በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ተደራሽ የሚሆንና ጥራቱም የተሻለ መሆኑን በማንሳት ከብሔራዊ ደህንነት አንጻር፣ ለሰላምና የአገራዊ እሴቶች በተሻለ መልኩ የሚንጸባረቁባቸው ጣቢያዎች እንዲፈጠሩም ያስችላል ነው ያሉት።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በአብዛኛው የናይል ሳትና የአረብ ሳት ሳተላይቶች ተጠቃሚዎች እንደነበሩ ያስታወሰው መግለጫው አሁን ላይ የራሳቸው የኮሙኒኬሽን ሳተላይት የሌላቸው አገራት እንደሚያደርጉት ኤስ.ኢ.ኤስ ከተባለው ኩባንያ ጋር በመስማማት ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የስርጭት መስመር እንዲኖራት መደረጉ ተነግሯል፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs