እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት አጠናክራ ስትቀጥል የሀማስ ታጣቂዎችም በእስራኤል ላይ በርካታ ሮኬቶችን ተኩሰዋል፡፡

እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት አጠናክራ ስትቀጥል የሀማስ ታጣቂዎችም በእስራኤል ላይ በርካታ ሮኬቶችን ተኩሰዋል፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱ የአየር ሀይልና የምድር ጦር የሀማስ ቡድን ላይ የተጠናከረ የአጸፋ ጥቃት መወሰዱን ገልጾ ነገር ግን ወደ ጋዛ ዘልቄ አልገባሁም ብሏል፡፡ ቢቢሲ የጋዛ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው በእስራኤልና በፍልስጤም ለቀናት ተባብሶ በቀጠለው ግጭት 1 መቶ 19 ፍልስጤማዊያንና 7 እስራኤላዊያን ተገድለዋል፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ሰርጥ የምናካሂደውን የአጸፋ ጥቃት አጠናክረን እንገፋበታለን ብለዋል፡፡ ሀሙስ እለት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር 9 ሺ ተጠባባቂ የሰራዊቱ አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ጥሪ ሲያቀርብ በጋዛ ሰርጥ ድንበር አካባቢም የጦር ሀይሉን እያጠናከረ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የሀማስ ቡድንን በእስራኤል ላይ በርካታ ሮኬቶችን መተኮሱንና የጀመረውን ጥቃት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs