ከስምንት አመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ የሚደረግ ታላቅ ፍልምያ

#ኢትዮጵያ ከስምንት አመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ የሚደረግ ታላቅ ፍልምያኮትዲቯር ከ ኢትዮጵያ ቦታ ፡- አቢጃን ስታድ ፍሌክስ ሁፌት ቦኚየጨዋታ ፡- 10 ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ2013 የአፍሪካ ዋንጫ መልስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አህጉራዊ መድረክ ለመመለስ እድል የሚፈጥረለትን ወሳኝ ጨዋታ ከሰዓታት መልስ 10፡00 ከኮትዲቯር አቻው ጋር ያደርጋል፡፡

በዚህ ተጠባቂ ጨዋታ ብሄራዊ ቡድኑ ካሸነፈ አሊያም አቻ ከተለያየ በቀጥታ ወደ ካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ የሚውሰደውን ትኬት መቁረጥ ይችላል፡፡የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቅርብ ባደረጋቸው 3 የአፍሪካ ዋንጫ እና የወዳጅነት ጨዋታዎች በድምሩ ተጋጣሚዎቹ ላይ 11 ግቦች ማስቆጠር ችሏል፡

በቅርብ ጊዚያት በመከላከል ብቃታቸው ጥሩ ብቃት እያሳዩ ያሉት ዋልያዎቹ በጨዋታዎች ግብ ከተቆጠረባቸው 270 ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡የኢትየጵያ ብሄራዊ ቡድን በዚህ አመት ካደረጋቸው ያለፉት 5 ጨዋታዎች 3ቱን ሲያሸንፍ በ1 አቻ ወጥቶ በአንዱ ብቻ ተሸንፏል፡፡እንደ ኤሮፒያን ዘመን ቀመር በ1968 የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በአፍሪካ ዋንጫው ያደረጉት ሁለቱ ሃገራት እስካሁን ለ4 ጊዜያት ያህል ተገናኝተዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ 2 ጊዚ ኮትዲቯርም 2 ጊዜ የተሸናነፉበትን ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ኳትዲቯር 8 ግቦችን ኢትዮጵያ ላይ ስታሳርፍ ኢትዮጵያ በአንጻሩ 4 ግቦችን ዝሆኖቹ ላይ ማስቆጠር ችላለች::

#ድል_ለኢትዮጵያ_ብሄራዊ_ቡድን#ኢቢኤስ#EBS