ከ1 ሺ በላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወስጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

#ከሃምሌ 2012 ዓ.ም እስከ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም ባሉት 9 ወራት #ከ1 ሺ በላይ #የዲሲፕሊን እርምጃ ወስጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ኮሚሽኑ ይህን ያለው መጪው አገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ለመግለጽ በሰጠው መግለጫ ሲሆን በከተማዋ ተንሰራፍቷል ተብሎ ከሚነገረው ህገወጥነት ጋር በተያያዘም የተለያዩ የማስተማርና የቅጣት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ለሚፈጸሙት ህገወጥ ድርጊቶች የራሱ የፖሊስ አባላትም ጭምር ተባባሪዎች ናቸው በሚል ትችቶች ሲሰነዘሩበት የቆየ ሲሆን አሁን ታዲያ በ9 ወራት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺ በላይ አባላቱን በህገወጥ ተግባር ላይ በማግኘቱ ተገቢውን ቅጣት መስጠቱን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡ምንም እንኳን በከተማዋ የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች ቢኖሩም ግን ካለው ነባራዊ ሁኔታ በተቃረነና በተጋነነ ሁኔታ ከተማዋ የወንበዴ መፈንጫ እንደሆነች በማስመሰል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሃሰተኛ መረጃን የሚያሰራጩ አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት መኖራቸውን ጠቅሶ እነርሱንም በህግ አግባብ እንደሚጠይቃቸው አስታውቋል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs