ከ32 በላይ ከተሞችን የሚያካልል የህዳሴ ጉዞ ሊደረግ ነው::

ለአንድ ወር የሚቆይ እና ከ32 በላይ ከተሞችን የሚያካልል የህዳሴ ጉዞ አሸኛኘት ተደርጓል፡፡ጉዞው ህብረተሰቡ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚያደርውን ተሳትፎ እንዲጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።”የህዳሴ ቱር” የተሰኘውን ዝግጅት የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህል እና ቅርስ አድን ድርጅት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ነው።ተባብረን ተደጋግፈን ከተጓዝን ከህዳሴ ግድብ ፍፃሜ ባለፈ የትም መድረስ ይቻላል ብለዋል የፅ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ።ዋና ዳይሪክተሩ ሀገሪቱ ያላትን እውቀት፣ ችሎታና ጀግንነት በማሰባሰብ መስራት ይገባልም ብለዋል።