“የማይስ ኢትዮጵያ”የኮንቬንሽን ቢሮ በይፋ ተመሰረተ::

ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ ጉባኤዎች እና ሁነቶች የቱሪዝም ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል የተባለው “የማይስ ኢትዮጵያ” የኮንቬንሽን ቢሮ በይፋ ተመሰረተ።

ምስረታው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቱሪዝም ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በተገኙ በት ነው ይፋ የሆነው።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ቢሮው መመስረቱ ታሪካዊ መሆኑን በመጥቀስ በአግባቡ ከተሰራበት ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።

ቢሮው በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የማይስ ቱሪዝም ወይም የጉባኤ፣ የየጉዞ ማበረታቻ፣ ኮንፈረንሶች፣ ሁነቶች እና አውደ ርዕይ መሰረት ያደረገ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል ተብሏል።

ተቋሙ “በምድረ ቀደምት እንገናኝ” የሚል መሪ ቃል እንዳለው ተገልጿል፡፡