የተሽከርካሪ አደጋ የሚደርስባቸው ዜጎች አስቸኳይና ነጻ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓት ይዘረጋል የተባለለት የአስቸኳይ ሕክምና መመሪያ ለመተግበር ስምምነት ተካሄደ።

ጤና ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስና የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ ለመተግበር የተስማሙበት ይህ የአስቸኳይ ህክምና መመሪያ ትግበራ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ዜጎች እስከ ሁለት ሺህ ብር የሚያስወጣ ሕክምናን በነጻ ማግኘት እንዲችሉ ያስችላል ተብሏል።

መመሪያውን በተመለከተ የጤና ተቋማት በአግባቡ ስለመተግበራቸው ክትትል ይደርጋል የተባለ ሲሆን የክልል ባለድርሻ አካላትም በጉዳዩ ላይ በጋራ ይሰሩበታል መባሉን ከኢዜአ ያገኘነው ዘገባ አመላክቷል።#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs