የታንዛኒያው ፕሬዘደንት ጆን ማጉፉሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ጆን ማጉፉሊ ዳሬሰላም በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ61 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።የፕሬዘደንቱን ህልፈት ያሳወቁት የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዘደንት ሳሚያ ሱሉሁ ናቸው።ህልፈታቸው ከልብ ህመም ጋር የተያያዘ መሆኑን ተነግሯል።ምንም እንኳ ሌሎች ወገኖች ፕሬዘዳንቱ በኮቪድ ሳቢያ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ቢገልፁም ።ማጉፋሊ ከ2015 ጀምሮ ነበር ታንዛንያን በፕሬዘዳንትነት የመሩት።