አዲስ ነገር – የትራንስፖርት ቢሮው ማሳሰቢያ

ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ በተገቢው መንገድ አገልግሎት የማይሰጡና የትራንስፖርት አገልግሎት በሚያቋርጡ ተሽከርካዎችና አሽከርካሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፡፡
የቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር እጸገነት አበበ ነገሩኝ ብሎ ኢቢሲ እንደዘገበው የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድጋፍ ሰጪዎችን ጨምሮ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በተመደበበት የስምሪት መስመር በመገኘት በተቀመጠው የታሪፍ መጠን ብቻ አገልግሎቱን መስጠት ይገባዋል፡፡
ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡን ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ፣ መስመር የሚያቆራርጡ፣ ታሪፍ የማይሰቅሉ ወይም የማይለጥፉና መሰል ድርጊት የሚፈጽሙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ካሉም ከወዲሁ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል፡፡
በጥናት መመለስ የሚገባቸው ጉዳዮች ካሉም ቢሮው አሰራሩን በመፈተሽ በሂደት ምላሽ እሰጣለሁ ማለቱ ተነግሯል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New