News

የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሰዓሊ ስዕል ሽያጭ

የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሰዓሊ ስዕል ሽያጭ

ትውልደ ኢትዮጵያዊዋ አርቲስት ጁሊ ምህረቱ በአፍሪካ አሜሪካዊያን ታሪክ ክብረ ወሰን በሆነ ክፍያ የስዕል ሥራዋ መሸጡ ተነገረ ።
ቢቢሲ እንዳለው የጁሊ ምህረቱ ረቂቅ ወይም አብስትራክት ስዕል በ10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ነው የተሸጠው ብሏል ።

በአክሬሊክ የስዕል ሥራ በቀለም የተሳለው ስዕል ዎከርስ ዊዝ ዘ ዳውን ኤንድ ሞርኒግ የተባለ ርዕስ የተሰጠው ነው።ጁሊ ምህረቱ በፈረንጆቹ 2005 የአሜሪካዋን የኒው ኦርሌንስ ከተማ ለመታው ሄሪኬን ካተሪና የሳለችው ረቂቅ ስዕል ነው አሁን ጨረታውን ያሸነፈው።

የጁሊ ምህረቱ ምርጥ ሥራ ለጨረታ ቀርቦ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው በኒውዮርክ የሶስዝባያ ጨረታ ላይ ነው።