የኒውዮርክ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ከእንግዲህ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የሚደረገው የፋይናንስ ምርመራ በወንጀል ላይ ያተኮረ ይሆናል አለ፡፡

የኒውዮርክ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ከእንግዲህ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የሚደረገው የፋይናንስ ምርመራ በወንጀል ላይ ያተኮረ ይሆናል አለ፡፡ የዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ሌቲታ ጄምስ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያ ላይ የተጀመረው የምርመራ ሂደት ከተራ የፍትሐብሔር ምርመራ ወደ ወንጀል ምርመራ አድጓል ብለዋል፡፡ዐቃቤ ሕግ ጄምስ ይሄን ያሉት የቀድሞውን ሪፐብሊካን ፕሬዝዳንት ከስልጣን በፊት የነበራቸውን የፋይናንስ ወጭና ገቢ ሲመረምሩ ከቆዩ በኋላ ነው፡፡ በሌላ በኩል ዶናልድ ትራምፕ በዴሞክራት ፖለቲከኛዋና ዐቃቤ ሕግ ጄምስ የሚደረገው ምርመራ የፖለቲካ በቀል ነው እያሉ ነው፡፡ ዐቃቤ ሕጓ በትራምፕ ኩባንያ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንዴት ከፍትሐብሔር ወደ ወንጀል እንደተቀየረ ግን ያብራሩት ነገር አለመኖሩን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡ ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።