የአውሮፓ ህብረት የ53 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል ፡፡

የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ክልልና ሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች የሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል 53 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል፡፡ የህብረቱ የአደጋ ጊዜ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺቺ ድጋፉ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስ የሚያስችል ነው ያሉ ሲሆን የሚረዱትም በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖች ይሆናሉ ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የህብረቱ ድጋፍ በተለያየ መልኩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳትና ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ እንደሚውልም አመልክተዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ የተባሉት ኮሚሽነሩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ስለሚፈፀም ጥቃት ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአውሮፓ ህብረት የኮሚሽን ባወጣው መረጃ አሳውቋል፡፡ መረጃው አክሎም ህብረቱ ለመሰል እርዳታ ባለፈው ዓመትም 10 ሚሊየን ዩሮ መለገሱን አስታውሷል፡፡#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs