የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ አደረገ።

የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ የሕፃናት መቀንጨር ችግርን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ አደረገ። የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሪት ያስሚን ወሀብረቢና የአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የባንኩ የኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብዱል ካማራ ተፈራርመዋል። የገንዘብ ድጋፉ በሕፃናት ላይ የሚታየውን የምግብ እጥረት ለመፍታት በኢትዮጵያ መንግሥት ይፋ የተደረገውን የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነትን ለማገዝ ያለመ ሲሆን ስምምነቱ ተግባራዊ በሚሆንባቸው በአማራና ትግራይ ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች ስራ ላይ የሚውል መሆኑም ተገልጿል።