የኢቢኤስ ስፖርት መረጃዎች

  • የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላለ ጉባኤውን የፊታችን ቅዳሜ ያደርጋል፡፡
  • የስፔኑ ሃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ለክልያን ምባፔ ዝውውር ይፋዊ የ160 ሚሊየን ዩሮ ለፓሪሴንት ጀርሜይን ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡
  • ቼልሲ ለኤርሊንግ ሃላንድ ይፋዊ ጥያቄ ያላቀረበው ወኪሉ ሚኖ ራዮላ ለተጫዋቹ አመታዊ 50 ሚሊየን ዩሮ ደሞዝ ለሱ ደግሞ ለወኪልነት 40 ሚሊየን ዩሮ በመጠየቁ እንደሆነ የጀርመኑ ቢልድ ዘግቧል፡፡
  • ሊቨርፑል የግራ መስመር ተከላካዩን አንዲ ሮበርትሰንን ውል እስከ 2026 አራዝሟል፡፡ ተጫዋቹ በሊቨርፑል ቆይታው የፕሪሚየር ሊግ እና የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፏል፡፡
  • የጁቬንቱሱ ኮከብ ክርስትያኖ ሮናልዶ የማንችስተር ሲቲን ዝውውር በተመለከተ ከፖርቱጋላዊያኑ በርናንዶ ሲሊቫ ሮበን ዲያዝ እና ጃኦ ካንሴሎ ጋር ንግግር ማድረጉን ለኪፕ አስነብቧል፡፡
  • አርሰናል የአትሌቲኮ ማድሪዱን የቀኝ ኬራን ትሪፔን ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ንግግር ማድረጉን ዩሮ ስፖርት ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡
  • ኢንተር ሚላን የላዝዮውን የፊት መስመር ተጫዋች ዩሃኪን ኮሪያን በ30 ሚሊየን ዩሮ የግሉ ለማድረግ ከጫፍ ደርሷል፡፡