የኢቢኤስ አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከፊቱ ላሉበት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይረዳው ዘንድ ከኡጋንዳ አቻው ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ የጨዋታው ቀን ለጊዚው ባይገለፅም የወዳጅነት ጨዋታው በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስቴዲየም እንደሚደረግ ግን ተረጋግጧል፡፡
  • ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚመጥን ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን አዲሱ የፈረሰኞቹ አለቃ ዝላትኮ ክራምፖቲች ተናግረዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትልቅ እና ታሪክ ያለው ክለብ ነው ያሉት አሰልጣኙ ይህንን ክለብ በማሰልጠኔም ደስታ ይሰማኛል ወደ ቀድሞ ውጤታማነት ዘመኑ ለመመልስ ከፍተኛ ጥረት አደርጋለው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
  • ኢትዮጵያ ተሳታፊ የምትሆንበት 18ኛው የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኬንያ አስተናጋጅነት ከፊታችን ረቡዕ አንስቶ ይደረጋል፡፡ ኢትዮጵያ በመድረኩ እስካሁን 98 ሜዳልያዎችን ባለፉት 17 ውድድሮች ያሳካችበት መድረክም በዚህም አመት ሲቀጥም 25 አትሌቶችን በ8 የውድድር መስኮች በአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ታሳትፋለች።
  • በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክብረወሰን በሆነ ዋጋ ሀሪ ኬን በመጪዎቹ ቀናቶች ማንችስተር ሲቲን ሊቀላቀል እንደሚችል ታማኙ ዴይሊ ቴሌግራፍ አስነብቧል፡፡ በቅርብ ካደረጋቸው 7 ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ የረታው እና በ3 ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር የተሳነው ማንችስተር ሲቲ ሀሪ ኬንን ወደ ክለቡ ለማምጣት ከ130 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ፈሰስ ሊያደርግ ነው፡፡
  • የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሊጎና ሶልሻየር የቡድኑ 5 ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾች ውላቸው እንዲራዘምላቸው ክለቡን መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ፖል ፖግባን ጨምሮ ሉክ ሾ እንዲሁም ሀሪ ማጓየር ማርከስ ራሽ ፎርድ በቲያትር ኦፍ ድሪምስ ረጅም ኮንትራት እንዲፈርሙ አሰልጣኙ የፈለጓቸው ተጫዋቾች ናቸው።
  • የክርስትያኖ ሮናልዶ የጁቬንቱስ ቆይታ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል፡፡ በጣሊያኑ ክለብ ውስጥ ደስታ እንደራቀው የተነገረለት ፖርቱጋላዊው ኮከብ ከሴሪያው ለቆ መሄድ እንደሚሻ ተሰምቷል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ዩናይትድ እና ፓሪሰነት ጀርሜይን የ36 አመቱን ኮከብ ፈላጊ ሆነው መቅረባቸው ተገልፅዋል፡፡
  • ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ለፓሪሴንት ጀርሜይን የመጀመሪያውን ጨዋታውን የሚያደርግበት ወቅት ይፋ ሆኗል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የለፓሪሲያኖቹ ንብረት መሆኑ የተረጋገጠው የ34 አመቱ አርጅንቲናዊው ከሁለት ሳምንታት መልስ ክለቡ ፓሪሴንት ጀርሜ ሬሜስን በስታድ ኦገስት ዴላኑ በሚገጥምበት የፈረንሳይ ሊግ ዓ ፍልምያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
  • አርሰናል ኖርዌያዊውን አማካይ ማርቲን ኦዴጋርድን በቋሚነት ለማዛወር እንቅስቃሴ መጀመሩን ዴይሊ ሚረር አስነብቧል፡፡ የፈጠራ ችግር በሜዳ ላይ እንዳለበት በጉልህ እየታየበት የሚገኘው ክለቡ ከሪያል ማድሪድ የ22 አመቱን ኮከብ በቋሚነት ለማስፈረም ውጥን ይዟል፡፡ ተጫዋቹ ሁለት ጎሎችን በውሰት ቆይታው ለአርሰናል ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
  • ባርሴሎና የአርሰናሉን ጋቦናዊ አጥቂ ፔየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ ፈላጊ ሆኖ መቅረቡ ተነግሯል ፡፡ ፊት መስመር ላይ ሁነኛ አገልግሎት የሚሰጣቸውን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የፈለጉት ብላግናራዎቹ የመድፈኞቹ አጥቂ ላይ አነጣጥረዋል፡፡ ለዝውውሩም ብራዚላዊውን ፍሊፕ ኮቲንሆን በልዋጭ ሊያቀርቡ መሆኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us