የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በምርጫው የመረጃ ነፃነት ህግ አተገባበርን አስመልክቶ መመሪያ በማዘጋጀት ስራ መጀመሩን አስታውቋል

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የመረጃ ነፃነት ህግ አተገባበርን አስመልክቶ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ መመሪያ በማዘጋጀት ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ተቋሙ መመሪያውን ያዘጋጀው በምርጫ ጊዜ የሰዎች መረጃ ማግኘት መብት መከበር ለነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ምርጫ እውን መሆን መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡ከምርጫው ጋር በተያያዘ የሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ትግበራ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች እንዲሻሻሉ የውሳኔ ሀሳብ ለማቅረብ መመሪያው ጠቃሚ እንደሚሆን አስታውቆ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ባለድርሻ አካላት ተቋሙ የክትትልና የድጋፍ ስራውን በሚሰራበት ወቅት ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የምርጫ ተዋናዮችና የምርጫ መረጃ የማድረስ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት በሙሉ የምርጫ መረጃዎችን ለአካል ጉዳተኞችና ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰቡ ክፍሎች እንዲያደርሱ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs