የኢትዮጵያ መርከብ በርበራ ወደብ መድረሷ ተነገረ

ከ20 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ መርከብ በርበራ ወደብ መድረሷ ተነገረ ። የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ንብረት የሆነችዉ “ጊቤ ” የተሰኘ ስያሜ የተሰጣት መርከብም 11 ሺህ 200 ቶን ስኳርና ሩዝ በመጫን ከ “ገልፍ ኢንዲያ ሰብ ኮንቲነንት ” ወደ በርበራ ደርሳለች። በቀጣይ ሳምንት ሸበሌ የተባለችው ሌላኛዋ መርከብ ተመሳሳይ ጭነት ጭና በርበራ ወደብ ትደርሳለች ተብሏል፡፡ ምንጭ ፡ ኢቢኤስ አዲስ ነገር