የኢትዮጵያ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በወዳጅነት አደባባይ መከበር ጀምሯል።

ኢትዮጵያ ሳምንት በሚል መጠሪያ በአይነቱ ልዩ ና ትልቅ የተባለለት አውደ ርዕይና ፌስቲቫል ዛሬ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ተከፈተ አውደ ርዕዩና ፌስቲቫሉን በባህልና ቱሪዝም እና በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን እንዲሁም በሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች በጋራ ትብብር አዘጋጅነት የተሰናዳ ስለመሆኑም ሰምተናል:: በዚሁ የኢትዮጵያ ሳምንት በሚል መጠሪያ በተከፈተው አውደርዕይ ላይ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድራት እንዲሁም የፌደራልና የክልል አመራሮችን ብሎም በአውደ ርዕይው የመክፈቻ ስነሥርዓት ላይ እንዲታደሙ ጥሪ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል:: በሚንስቴር መስሪያ ቤቶቹ የጋራ ትብብር የተከፈተው ይሄው የኢትዮጵያዊያን ባህል ታሪክ እንዲሁም እሴቶች ለእይታ የሚያበቃው አውደ ርዕይና ፌስቲቫል ከዛሬ ግንቦት 10 ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችለሏል::