የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በነገው እለት የቻን የቅድመ ማጣርያ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያደርግ ይሆናል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በነገው እለት የቻን የቅድመ ማጣርያ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያደርግ ይሆናል::
በመጪው አመት ጥር ወር ላይ በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ለመሳተፍ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታድየም ከሃምሌ 6 ጀምሮ ዝግጅቱን ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በትላንትናው እለትም ጨዋታው ወደ ሚካሄድበት ታንዛኒያ ማቅናቱ ይታወቃል፡፡

በሀገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት ይህ ውድድር በየሁለት አመቱ የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩ ከተመሰረተም 13 አመታትን ብቻ አስቆጥሯል፡፡ ሞሮኮ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ በቻን ውድድር ሁለት ሁለት ዋንጫዎችን በመውሰድ ሃያልነታቸውን ሲያስመሰክሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ በውድድሩ በ2014 እና 2016 ተሳትፎዋን አድርጋለች፡፡ በውድድሩ ሁለት ጊዜ መንገስ የቻለችው ሞሮኮ በ 2018 እርሷ አዘግጅታ ዋንጫውን ማሸነፍ የቻለች የመጀመሪያዋ ሃገር መሆኗ ይታወቃል፡፡

በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ከምድብ ማጣርያ ጨዋታዎች ባለፍ ብዙ ርቀት ተጉዛ የማታውቀው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን በነገው እለት ሃምሌ 15 የምታደርግ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ከ 6 ቀናት በኋላ በዛው በታንዛኒያ የሚከናወን ይሆናል ይህንን ተከትሎም ብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅቱን በዳሬሰላም እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሀገር ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ስለ ተጋጣሚያቸው ደቡብ ሱዳን ሰፊ የሆነ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉና ለዝግጅት የነበራቸው ጊዜ አጭር መሆኑን በመግለጽ ተጫዋቾችን ከውድድር ወደ ውድድር መልሶ መክተቱ ፈታኝ መሆኑንም መናገራቸው አይዘነጋም
ሪፖርተር፡ ሳምራዊት ሐብቴ

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS